ለዘመናት የሀገራችን ክብርና ሉዓላዊነት ልናስከብር የቻልነው ባለን የማይናወጥ ጽናት ነው።     ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

በአድዋ ድል መታሰቢያ በፀጥታና ደህንነት ተቋማት የተዘጋጀ ጷጉሜን 01 የጽናት ቀን በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ መክፈቻ ለይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት 
የኢፌዴሪ የመከላከያ ሚኒስትርና የበዓሉ አዘጋጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ፅናት የታሪካችን አካል ፣የኑሯችን ዘይቤ ለትውልዱ የምናወርሰው አኩሪ ዕሴታችን ነው ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር በፅናት ሀገራቸውን ላገለገሉ ክብር የሚሰጥበት ፣ ያለንን የፅናት ጥንካሬ የምናስቀጥልበትና ለመጭው ትውልድ የምናወርስበት መሆኑን ገልፀዋል።

ቀኑን ስናከብር የኢትዮጵያ መልክ የሆነውን ፅናት ተላብሰን ያስመዘገብናቸውን ድሎች ለማስቀጠልና የሚገጥሙ ፈተናዎችን ወደ መልካም ዕድል በመለወጥ ሀገራችንን ወደ አዲስ ብሩህ ተስፋ ለማሸጋገር የምንሰራበትም ሊሆን ይገባል ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

በዝግጅቱ ላይ የጦር ኃይሎች ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጀኔራል አበባው ታደሰን  ጨምሮ የቀድሞ የሀገራችን ፕሬዝዳንት ክቡር ዶክተር ሙላቱ ተሾመ፣ ሚኒስትሮች ፣የፀጥታና ደህንነት ተቋማት አመራሮች የስራ ሀላፊዎች፣  ከፍተኛ የመከላከያ ሰራዊቱና የፌዴራል ፖሊስ አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በዝግጅቱ ላይ በፀጥታ ተቋማቱ የተዘጋጀ የዲጅታል ኢግዚቢሽን ቀርቧል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
SS1
ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ሀይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ።     ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
SSS
የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ASH
የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ