ኢትዮጵያ እና ኬንያ ከ62 አመት በኋላ Defence Cooperation Agreement (DCA)  ወታደራዊ የትብብር ስምምነት ለ2ተኛ ጊዜ ተፈራረሙ ።

የተደረገው ኢትዮጵያና ኬንያ እ.ኤ.አ 1963 ኬንያ ነፃነቷን ባገኘችበት ዓመት December 12, 1963 ከተፈራረሙበት በኋላ ለ2ተኛ ጊዜ መከላከያ ለመከላከያ የተደረገ ታላቅ ወታደራዊ ስምምነት ነው፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና የኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም ጄነራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መስራት በሚቻልባቸው መስኮች ወታደራዊ የትብብር ስምምነት (DCA) ተፈራርመዋል ።

ወታደራዊ የትብብር ስምምነት Defence Cooperation Agreement (DCA) እንደሌሎች ስምምነቶች የሚታይ ስምምነት ሳይሆን ስትራቴጂካዊ በሆኑ ስራዎች ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ሃገሮች በመሃከላቸው ያለው ግንኙነትና መተማመን በሚያድግበት ወቅት የሚፈፀም ነው፡፡

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ እና ኬንያ  የቆዬ ታሪካዊ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል።

የኬንያና የኢትዮጵያ መከላከያ ተቋማት በተለያዩ ወታደራዊ መስኮች በትብብር እየሰሩ መምጣታቸውን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ በቀጣይም በጋራ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነው የገለፁት።

ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከኬንያ መከላከያ ኢታማዦር ሹም  ጋር  Intelligence sharing ፤ በጋራ ወታደራዊ ልምምድ ፤ በስልጠና በወታደራዊ ኢንዱስትሪ፣ ሽብርተኝነትን በመዋጋት፣ በድንበር ደህንነት እና በሌሎችም ተያያዥነት ባላቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተፈራርመናል ብለዋል ።

በተጨማሪም ክቡር ፊልድ ማርሻሉ በስምምነቱ ከሃገራቱ በተጨማሪ በቀጠናው ሰላምና ደህንነት ላይ በጎ ተፅዕኖ የሚፈጥሩ በርካታ ስራዎችን አብረን እንሰራለን ብለዋል፡፡

የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ ለዕርሳቸውና ለልዑካን ቡድናቸው ለተደረገላቸው ደማቅና የሞቀ አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

የኬንያ መከላከያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ካሃሪሪ የኢትዮጵያ እና የኬንያ ግንኙነት ከታሪክም ባለፈ በባህል፣ ህዝብ ለህዝብ እና በጅኦግራፊ ላይም የተመሰረተ እንደሆነ ተናግረዋል ።
ጄኔራል መኮንኑ ኢትዮጵያና ኬንያ ያደረጉት ወታደራዊ ስምምነት ከሁለቱ ሀገራት ባለፈ ለቀጠናው ሰላምና መረጋጋትም የጎላ ፋይዳ እንዳለው ገልፀዋል።

ጄኔራል ቻርልስ ሙሪዩ ለወደፊትም ከኢትዮጵያ መከላከያ ጋር በትብብር በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ የኬንያ መከላከያ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶግራፍ ፍቃዱ በቀለ

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።