118ኛው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ቀን በዓል ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ የባህር ሀይል አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ባስተላለፉት መልዕክት ፣ የለውጡ መንግስት የባህር በር አስፈላጊነት ላይ ባለው የፀና አቋም እና የመከላከያ ሰራዊቱ ስትራቴጂ አመራሮች ባደረጉት ድጋፍና ክትትል የአንጋፋውን የኢትዮጵያ ባህር ሀይል ወደ ቀድሞ ገናና ስሙ ለመመለስ የተሰሩት ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የገጠሟትን ፈተናዎች በድል እየተወጣች የመጣች ታሪካዊና ቀደምት ሀገረ መንግስት መሆኗን አውስተው የባህር በር ጥያቄው የኢትዮጵያ የህልውና ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
ባህር ሀይሉ ራሱን ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች ፣ የተቋማት ግንባታ ከማሳደጉም ባለፈ የመነሻ የዉጊያ ትጥቆች ማሟላቱንም ተናግረዋል።
የባህር በርና ባህር ሀይል የማይነጣጠሉ መሆናቸውን የገለፁት ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ ሀገራችን ባላት ታሪክና መብት የባህር በር የማግኘት ጉዳይ የህልውና ጉዳይ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ሀገራችን የባህር በር ለማግኘት የምታደርገውን ፍትሃዊ ጥያቄ ለጋራ ተጠቃሚነት በሰጥቶ መቀበል መርህ መስራት እንደሚገባም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ተሠማ ኡርጌሳ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





