በሶማሊያ ሴክተር 3 የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የ18 ወራት ተልዕኳቸውን አጠናቀው ተመለሱ፡፡

በሶማሊያ ሴክተር ሦስት 5ኛ ዙር ብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት የተሰጣቸውን ሃገራዊና አህጉራዊ ተልዕኮ በማጠናቀቃቸው ሴክተሩ የሽኝት ስነ-ሥርዓት አድርጎላቸዋል፡፡

በዚህ የሽኝት ስነ-ሥርዓት ላይ የሴክተር 3 ዋና አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ተክሉ ሁሪሳ የምስጋና ሰርተ-ፊኬት ከሰጡ በኋላ 5ኛ ዙር ብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን አባላት ሀገራችንና መንግስታችን የሰጣችሁን ተልዕኮ በስኬት በማጠናቀቃችሁ ልትደሠቱ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የሴክተሩ ሁለንተናዊ ወትሮ ዝግጁነትን በማጠናከርና ራሳችንን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንድንገኝ ማስቻላችሁ፣  ከሴክተሩ ሞያተኞች ጋር በጋራ በመሆን በተለያየ ምክንያት ከስራ ውጪ የነበሩትን ብረት ለበስ፣ተሸከርካሪዎችን፣ከነፍስ ወከፍ እስከ የውጊያ ድጋፍ መሳሪያዎችን እና ሌሎች ንብረቶች  ጠግናችሁ ለሥራ ዝግጁ ማድረጋችሁ፣ ሐገራችን ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ገቢ እንድታገኝ አሥችሏችኋል ብለዋል።

ብርጋዲየር ጄኔራል ተክሉ ሁሪሳ ብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ኢትዮጵያ በሠላም ማሥከበር ተልዕኮ ያላትን ከፍተኛ ተቀባይነት በማሥቀጠሉ ረገድ የበኩላችሁን ተወጥታችኋልና እናመሠግናለን ብለዋቸዋል።

ከሃገራችን ተቀብለን የመጣነውን ተልዕኮ በጥሩ ወታደራዊ ሥነ-ምግባር እና ያለደከመኝ ሰለቸኝ ተቀብለን የሚጠበቅብንን ሁሉ መፈፀም በመቻላችን ደስተኞች ነን ያሉት ደግሞ የብሄራዊ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ሃላፊ  ኮሎኔል ገረመው ገመዳ ናቸው። በነበረን የ18 ወር የተልዕኮ ጊዜ ከሴክተሩ ሞያተኞች ጋር በመሆን በርካታ ሥራዎችን በመስራት የሰራዊታችንን ወትሮ ዝግጁነት ማጠናከር ችለናል ሲሉም ገልፀዋል፡፡

ዘጋቢ ሰመረ እሸቱ
ፎቶግራፍ አይናለም ተክለፃዲቅ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ