የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማህበር ተቋም የስራ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ባካሄደበት በዛሬው ዕለት በክብር እንግድነት የተገኙት የመከላከያ ሚንስቴር ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በመከላከያ ሠራዊታችን አባላት ተሳትፎ የተቋቋመው የአድዋ ድል ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሰራዊታችን የአገራችንን ዳር ድንበርና ሉአላዊነት የሚጠበቅ ብቻ ሳይሆን የልማት ዋና አካል መሆኑንም በተጨባጭ የሚያሳይ ነው ብለዋል።
ይህ ኢንቨስትመንት ከካፒታልም በላይ ስለሆነ አብረን የገነባነውን ተቋም ስኬት ለማረጋገጥ ቁርጠኝነትና የጋራ ጥረት ይጠይቃል ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ካፒታሉን በማሳደግና ተወዳዳሪነቱን በማጠናከር የመከላከያ ሰራዊታችንን ቤተሰብ ክብርና ኩራት ሆኖ የሚያገለግል ተቋም እንዲሆን ሁላችንም ከልብ መረባረብ አለብን ሲሉም አሥገንዝበዋል፡፡

አክሲዮን ማህበሩ ባለቤትነቱ አክሲዮን ለገዙት ብቻ ሳይሆን ለመላው የሰራዊታችን አባላት ሁሉ ጭምር ነው፤ በሮቹም የዕድገትና የአንድነት ራዕይን ለሚደግፋ ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ክፍት ነው ሲሉ ኢንጂነር አይሻ ገልፀዋል።
ባለአክሲዮኖች ሆናችሁ የተቀላቀላችሁ የመከላከያ ሠራዊታችን አባላትና ቤተሰቦች እንዲሁም ማህበሩን ለማጠናከር እክሲዮኖችን ለገዛችሁ ሁሉ በቃላት ብቻ ሳይሆን ትርጉም ባለው እርምጃ ከሠራዊታችን ጎን በመቆም የድጋፋችሁ እና የአብሮነታችሁ ማሳያም ጭምር ነውና ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ብለዋል።
ይህ ተቋም የተቋቋመበት ዓላማ ሙሉ በሙሉ እውን አንዲሆነ በቁርጠኝነትና በአጋርነት መንፈስ መሥራት እንደሚገባ እደራ ለማለት እወዳለሁ ያሉት ክብርት ሚኒስትሯ ይህን እክሲዮን ማህበር ማሳደግና ማሳካት የመከላከያ ሰራዊታችን እና ህዝባችን በእንድ ዓላማ ሲተባበር በጀግንነት ሁሉንም እንደሚወጣ ማሳያም ጭምር ስለሆነ እኛም አንድ ሆነን በአድዋ እንዳስመዘገብነው ድል በጋራ ሆነን የአክሲዮን ማህበራችንን ስኬት ማረጋገጥ ይገባናል ሲሉ አሥገንዝበዋል።
ዘጋቢ ራሔል ዮሐንስ
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ቴሌግራም
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official





