ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።

ሁለቱ ሃገራት በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ የሁለትዮሽ ውይይት ካካሄዱ በኋላ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ እና የኮንጎ ሪፐብሊክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በይፋ የተመሰረተው ኮንጎ ነፃነቷን ካገኘች በኋላ ነው።

ኢትዮጵያ በወቅቱ በአፍሪካ የነፃነት ንቅናቄ ውስጥ ትልቅ ሚና የነበራት በመሆኗ፣ ኮንጎ ሪፐብሊክ ነፃነቷን ባገኘችበት በ1960ዎቹ መጀመሪያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በይፋ መሥርታለች።

ግንኙነቱ በዋናነት የተጀመረው በዓለም አቀፍ መድረኮች በተለይም በአዲስ አበባ በተመሠረተው በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (OAU) እና በአሁኑ  የአፍሪካ ኅብረት (AU) ማዕቀፍ ውስጥ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ኢትዮጵያና ኮንጎ ሪፐብሊክ ረጅም አመታትን ያስቆጠረ ጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ገልፀዋል ።

ኢንጅነር አይሻ ከኮንጎ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስትር ጋር በዋናነት በወታደራዊ ኢንዱስትሪ ውጤቶች  ፣ በጦር መሳሪያ ጥገና ፣ በትምህርትና ስልጠና እና በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ገልፀዋል።

ስምምነቱ የሁለቱን ሃገራት ወታደራዊ አቅም በጋራ ለመጠቀም የሚያስችል እድል ይፈጥራል ብለዋል።
አሁን ያለንበት አለም በትብብር መስራትን ይጠይቃል ያሉት ክብርት ኢንጅነር አይሻ ድንበር ዘለልና ሽብርተኝነት የመሳሰሉ ቀጠናዊ ችግሮችን በጋራ  ለመከላከልም ከፍ ያለ በጎ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ከሌሎች አገራት ጋር የሚኖረን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ክብርት ሚኒስትሯ ተናግረዋል።

የኮንጎ ብራዛቢል መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር  ቻርለስ ሪቻርድ ሞንጆ በበኩላቸው ስምምነቱ የሁለቱን ሃገራት ሰላምና ደህንነት የበለጠ ለማጎልበት የጎላ ፋይዳ እንዳለው ተናግረው የመግባቢያ ስምምነቱን ወደ ተግበራ ለመቀየር  በቅርቡ ወደ ተጨባጭ ስራ እንገባለን  ብለዋል።

የኮንጎ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ቻርለስ ሪቻርድ ሞንጆ ለክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድድ ኮንጎ ብራዛቢልን እንዲጎበኙም  ግብዣ አቅርበውላቸዋል ።

የመከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሃመድ ለኮንጎ ሪፐብሊክ መከላከያ ሚኒስቴር ሚኒስትር የተለያዩ ስጦታዎችን ያበረከቱ ሲሆን በተመሳሳይ የኮንጎ መከላከያ ሚኒስትር ቻርለስ ሪቻርድ ሞንጆ ያዘጋጇቸውን ስጦታዎች ለኢንጅነር አይሻ መሃመድ ሰጥተዋል።

ዘጋቢ በላቸው ክንዴ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ
SS1
ከተጣሉበት በማንሳት በራስ አቅም ተሻሽለው ወደ ሀይል የገቡት ትጥቆች የተቋሙን የውጊያ አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራሉ።     ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
SSS
የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።
ASH
የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ