የውስጥ አቅሞችን አሟጦ በመጠቀም ለተቋማዊና ሀገራዊ ጥቅም ማዋል ይገባል።  ክብርት ኢንጅነር አይሻ መሀመድ

በሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጉብኝት ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ አንጋፋው ኮሌጅ ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የሙያ ተቋምና ሀገራዊ አቅም እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

ኮሌጁ ዘመኑ የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ ራሱን ማዘጋጀት እንደሚገባው የገለፁት ሚኒስትሯ የስራ ፈጠራን ከሃሳብ እስከ ውጤት በተቋሙ ኢንዱስትሪዎችና ወደ ምርት የሚለወጡበትን ዕድል ማመቻቸት እንደሚገባም ተናግረዋል።

የተቋሙን ባህሪና ሁኔታ የተረዱ ባለሙያዎችን ማፍራት ወሳኝ መሆኑን የጠቆሙት ሚኒስትሯ በተለይም በግንባታ ፤ በፊኒሽንግና በዲዛይን ባለሙያዎችን ማፍራት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሀላፊ ጀኔራል ይመር መኮንን በበኩላቸው ፣ሰራዊቱን በቴክኖሎጂና በሰው ሀይል ለማዘመን ከተያዘው ዕቅድ አንፃር ኮሌጁን ዘመኑ የደረሰበት ደረጃ ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

የመከላከያ ኢንተርፕረነርሺፕና ኢኖቬሽን ማዕከልን ከኮሌጁ ጋር ማስተሳሰር አዋጭ በመሆኑም በጋራ የሚሰሩበት ሁኔታ እየተመቻቸም እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

በኮሌጁ ያሉ አቅሞችን በመጠቀም ለውጊያ አቅም  የሆኑ ሙያተኞችን በማፍራት፣ የተለያዩ የተሽከርካሪና የጦር መሳሪያ መለዋወጫን ከማምረት ባለፈ ለተቋሙ ለሀገርና ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥቅም እንዲሰጥ እየተሰራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

በኮሌጁ የተገኙ ለውጦችን በማጠናከርና ለፈጠራ ትኩረት በመስጠት ለተቋሙ ተልዕኮ አጋዥ ሁኔታ ለመፍጠር ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

ወቅታዊ አጀንዳ

p
የኢትዮጵያ ሠላም አሥከባሪ በማንኛውም አይነት ፈታኝ ሁኔታ ሳይረታ ተልዕኮውን እየተወጣ ነው፡፡   ብርጋዴር ጄኔራል ሺሺር ባራድዋጅ
m
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ከሪፖርታጅ ፕሮፐርቲ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ስምምነት ተፈራረመ።
j
የመከላከያ ሠራዊት ፋውንዴሽን ያስመዘገበውን አስደናቂ ለውጥ ይበልጥ ማጠናከር ይገባል፦    ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።