የባሕልና ስፖርት ሚኒስቴር የኪነ ጥበብና ስነ ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ መክዬ መሃመድ የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሀላፊ ብርጋዲየር ጀኔራል ይታያል ገላው የመከላከያ ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከልን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ወቅት የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር የኪነ ጥበብ ስነ ጥበብ ፈጠራ ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባየ ሠራዊቱ ለሀገሩ የሚሠዋ የሀገር ፍቅር መለያ በመሆኑ ይህን ሠራዊት የሚገልፅ የኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከሉ እየሠራ እንደሚገኝ በጉብኝቱ ማየታቸውን ተናግረው እንደ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ተገቢው ድጋፍ ለማዕከሉ እንደሚደረግ አረጋግጠዋል።
የመከላከያ ጥናትና ምርምር ማዕከል ሀላፊ ብርጋዴር ጀነራል ይታያል ገላው በበኩላቸው ተዋግቶ የሚያሸንፍ ሠራዊትን ለመገንባት የመከላከያ ስፖርት እና ኪነ ጥበብ ስራዎች ማዕከል ሚና የጎላ በመሆኑ ማዕከሉ እየሠራ ያለውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
በጉብኝቱ የማዕከሉ የስራ እንቅስቃሴ እና የምስረታ ታሪክ ለክብር እንግዶች ገለፃ የተደረገ ሲሆን የክብር እንግዶችም የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል።






