የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የሠራዊቱን አቅም እየገነባ ይገኛል።     ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም

የመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ አመታዊ የስራ እንቅስቃሴዎቹን አስመልክቶ የማጠቃለያ መርሃ ግብር አከናወነ።

ዋና መምሪያው በአመቱ በተለያዩ የተቋሙ ክፍሎች ያከናወናቸውን የመሠረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በፎቶ አውደ ርዕይ መልኩ አስጎብኝቷል።

በመከላከያ መሃንዲስ ዋና መምሪያ የማጠቃለያ መርሃ ግብር ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ዋና መምሪያው የተቋሙ ሪፎርም ዋና አካል ስለመሆኑ ተናግረዋል።

የመሃንዲስ ዋና መምሪያ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ዋና መሠረት ስለመሆኑም አንስተዋል።

ሰራዊታችን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ መጠናቀቅ ከባድ የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የጠላትን ሴራ በማክሸፍ የሀገራችንን ትንሳኤ ስለ ማብሰሩ ገልፀዋል።

በቀጣይም ለሀገራችን እድገት በታላቅ የዝግጁነት መንፈስና ቁርጠኝነት የበለጠ ታሪክ ለመስራት  ሰራዊታችን ዝግጁ ሊሆን እንደሚገባም ተናግረዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የመሃንዲስ ዋና መምሪያው ያሉትን ጥንካሬዎች በማቀብ ለቀጣይ የተቋሙን የፕሮፌሽናል የግንባታ ሂደት የማጠናከር ተግባሩን በቆራጥነት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም የስራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።

ዋና መምሪያው በአመቱ ለተከናወኑ አመርቂ ውጤቶች አብላጫ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ክፍሎች እና አባላቱ የሽልማትና እውቅና መርሃ ግብር አከናውኗል።

ዘጋቢ ራሔል ገዛኸኝ
ፎቶግራፍ ፉራ አብደላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።