የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ ነው።   አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም

በ2012 ዓ.ም እንደገና ወደ ስራ እንዲመለስ የተደረገው እና በአዲስ መልክ የተደራጀው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ለሀገር በሚያበረክታቸው ወታደራዊና ኮሜርሻል ምርቶቹ አማካኝነት በ2017 ዓ.ም ከኮርፖሬሽን ወደ ግሩፕ ያደገ የሀገር ሀብት ነው።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ በአዲስ አመራር ተደራጅቶ ወደ ምርት እንዲገባ ከተደረገ በኋላ ወደ ትርፋማነት ተሸጋግሯል። እየተመዘገበ ያለውን ለውጥም በጥናት እና ምርምር አስደግፎ መቀጠል ችሏል።

በትናንትናው ዕለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በተገኙበት ሰባተኛው ታማኝ ግብር ከፋዮች የእውቅና ሥነሥርዓት ላይም ኢንዱስትሪ ግሩፑ አንዱ ለመሆን በቅቷል።

በዚሁ ሀገራዊ የዕውቅና እና የምስጋና መድረክ የመከላከያ ኢንጅነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ መከላከያ እያደረገ ያለውን ሪፎርም ተከትሎ ከኪሳራ ወደ ትርፋማ በመሸጋገር በኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶክተር) የታማኝ ግብር ከፋይ የወርቅ ሽልማት ተበርክቶለታል።

ይህም ውጤት የመከላከያ ሪፎርም ስለመሳካቱ አንዱ አመላካችና ግሩፑም መንግስትና ሀገር በሚፈልገው መንገድ ላይ መሆኑን ያመላክታል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ አቶ ጌታቸው ኃይለማርያም ለመላው የኢንዱስትሪ ግሩፑ አመራር እና ሠራተኞች እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ የተበረከተው ሽልማት የሁሉንም አመራር እና ሠራተኛ ሞራል እና ተነሳሽነት የሚያሣድግ ነው ብለዋል።

የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪ ግሩፕ የሠራዊቱን ዝግጁነት ለማረጋገጥ ሚናው ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት ዋና ሥራ አሥፈፃሚው በቀጣይም ወታደራዊ እና ስቪል ምርቶችን ዘመናዊነትን በተከተለ አግባብ እንደሚያሥቀጥል ተናግረዋል።  ዘገባው የመስከረም ብርሃኔ ነው
 
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።