ሰላም ፣ ልማትና የባህር በር ባለቤትነታችንን እናረጋግጣለን!!    ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ 

በኢትዮጵያ ባህር ሀይል ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት  በተከበረው 118ኛ የመከላከያ ሠራዊቱ ቀን በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ ሀገራችን የተፈጥሮ ሀብቷን እንዳትጠቀም በውስጣዊ  ግጭት  እንድታተኩርና ለዘመናት በድህነትና ኋላቀርነት እንድትቆይ የሚፈልጉ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ሴራ  በጀግናው ሰራዊታችን ጀግንነት ፣ በመላ ህዝባችን ድጋፍና በመሪዎቻችን በሳል አመራር ሰጭነት በመበጣጠስ ወደ ሰላምና ልማት እየተሸጋገርን እንገኛለን ብለዋል።

የተፈጥሮ ሀብታችንን ተጠቅመን እንዳንበለፅግ የሚሰሩ ታሪካዊ ጠላቶቻችንና የባዕዳን አቤት ባይ  ሀይሎችን እኩይ ሴራ በማክሸፍ የልማት ፣ የሰላምና የመንሰራራት መንገዳችንን ጀምረናል ሲሉም ገልፀዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በዓሉ ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሞከሩ ሀይሎች ፈርሰው ፣ የሀገርና የተቋማችን ሁለንተናዊ አቅም እየጨመረ በመጣበት ወቅት የምናከብረው መሆኑም ለየት ያደርገዋል ነው ያሉት።

ኢትዮጵያ ነፃነቷና ሉአላዊነቷ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር  ብዙ መስዋዕትነት ከፍላ ዛሬ የደረሰች መሆኗን የገለፁት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የዚህ ትውልድም ጥያቄ የሆኑትን የሰላም የልማትና የባህር በር ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ያሳካል ብለዋል።

ላለፋት ሰላሳ ዓመታት ተኝተናል ፣ አሁን ግን ላንተኛ እንደሀገር ነቅተናል ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ የሀገራችን የህልውና ጥያቄ የሆነውን የሰላም ፣ የልማትና የባህር በር ተጠቃሚነት እናሳካለን ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህም ለመላው የመከላከያ ሰራዊቱ አመራሮችና አባላት ኢትዮጵያ እንደምታመሠግናቸው አሥታውቀዋል።

በዚህ ትውልድም የሚያሴሩብን ታሪካዊ ጠላቶችና ባንዳዎች  ሀገራቸውን ለማዳከም ቢሞክሩም በጀግናው ሰራዊታችንና በህዝቡ ድጋፍ ሀገራችን ወደ ተሻለ ሰላምና ዕድገት እያመራች እንደምትገኝ ተናግረዋል።

የሀገር መከላከያ ሰራዊታችንን በማጠናከር ፣ ሰላማችን እና  የባህር በር ባለቤትነታችንን ለማረጋገጥ የሚያስችል ቁመና ላይ እንገኛለን ብለዋል።

በዝግጅቱ ላይ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር ሀይሻ መሃመድን ጨምር ከፍተኛ የሰራዊቱ አመራሮች፤ የቀድሞ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታሞዦር ሹም ጀነራል ሳሞራ የኑስ ፣የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ፣ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደርና ወታደራዊ አታሼዎች ፤ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰራዊት አመራሮች ፣ የጀግኖች አባት አርበኞች ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን ፣ አባገዳዎችና ሀደ ስንቄዎች ፣  የመከላከያ የክብር አባላት ፣ የቢሾፍቱ ከተማ አመራሮች የሀገር ሽማግሌዎችና የከተማው ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ተሰማ ኡርጌሳ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።