የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ታላላቅ የሀገር መሪዎችን ማፍራት የቻለ ነው።

የኢፌዴሪ ስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ፣ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሃመድ  የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ሃላፊ ጀኔራል ይመር መኮነን የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚን ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ የአካዳሚውን አሁናዊ የመማር ማስተማር ሂደት በመመልከት በቀጣይ ለሚያከናውናቸው የትምህርትና ስልጠና ስራዎች ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ ያለመ  ነው።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ለአካዳሚው አመራር እና አባላት እንዲሁም በስልጠና ላይ ለሚገኙ ዕጩ መኮንኖች ባስተላለፉት መልዕክት “የሰው ልጅ በዓለም ላይ ከሃብት እና ንብረት የበለጠ ምን ይሰጥህ ቢባል በህይወት መኖር” ብሎ ይመልሳል  እናንተ ጀግኖች ግን መተኪያ የሌለውን ህይወታችሁን ለምተወዷት ሃገራችሁ ያለስስት የምትሰጡ በመሆናችሁ እንኮራባችኋለን ሲሉ አክብሮታቸውን ገልፀዋል።

የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው ይህ አንጋፋ ወታደራዊ አካዳሚ ላለፉት 91 ዓመታት በዘለቀው የትምህርትና ስልጠና ተግባሩ የኢትዮጵያን ሉአላዊነት በጀግንነት ያስከበሩ መሪዎችን ከማፍራት ባለፈ ሃገር የመሩ መሪዎችን መፍጠር የቻለ ብርቅዬ ወታደራዊ አካዳሚ ነው ብለዋል።

ኢንጂነር አይሻ እናንተ በዚህ አንጋፋ ወታደራዊ አካዳሚ የመማር እድል ያገኛችሁ ወጣት ዕጩ መኮንኖች ያገኛችሁትን እድል በአግባቡ በመጠቀም ራሳችሁን በዕውቀት፣ በክህሎትና በአስተሳሰብ አሳድጋችሁ የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያን ለመምራት ራሳችሁን ማዘጋጀት ይገባችኋል ሲሉ አስገንዝበዋል።

የአካዳሚውን የመማር ማስተማር አሁናዊ ሁኔታ
በተመለከተ ገለፃ ያቀረቡት የአካዳሚው አዛዥ ብርጋዲየር ጀኔራል ጌታቸው ሃብታሙ አካዳሚውን በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ2030 ዓ.ም በአፍሪካ የልህቀት ማዕከል ለመሆን አስቦ እየሰራ እንደሚገኝ ለከፍተኛ አመራሮቹ አስረድተዋል።

ዘጋቢ ፍቃዱ ጆቴ
ፎቶግራፍ ነጋሽ ደጀኔ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።