የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለተቋምና ለሀገር የሚሠጠውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።

የኢፌዴሪ የስራና ክህሎት ሚንስቴር ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪያት ከሚል፤ የመከላከያ ሚኒስትር ክብርት ኢንጅነር አይሻ አህመድ እና የመከላከያ ትምህርትና ስልጠና ዋና መምሪያ ኃላፊ ጀኔራል ይመር መኮንን አንጋፋውን የሜጄር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ጎብኝተዋል።

ኮሌጁን ተዘዋውረው የጎበኙት ክብርት ሙፈሪያት ከሚል ኮሌጁን የልዕቀት ማዕከል ከማድረግ ባለፈ በሙከራ ላይ ያሉ ፈጠራዎችን ወደ ምርት በመለወጥ ለሀገርና ለተቋም የሚሰጡት ዕምቅ አቅም መኖሩን መረዳታቸውን ገልፀዋል።

ለተቋምና ለሀገር አንጋፋና ታሪካዊ የሆነው ኮሌጁን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በጋራ መስራት እንደሚገባ የገለፁት ሚኒስትሯ ለዚህም ተቋማቸው በስልጠና ፣ በሰው ሀይል ግንባታና በቴክኖሎጂ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ኮሌጁን ከመከላከያ ኢንተርፕርነርሺፕና ኢኖቬሽን ማዕከል ጋር በማቀናጀት ለተቋሙና ለሰራዊቱ ጥቅም ለመስጠት ምቹ መደላደል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኮሌጁ ያለውን አሻራ በመጠቀም ለወደፊቱ የሚዘጋጅ ወታደራዊ የቴክኒክ ኮሌጅም ለማድረግ ርብርብ ሊደረግ እንደሚገባም ተናግረዋል።

በጉብኝቱ ላይ በኮሌጁ መምህራንና ተማሪዎች የተሰሩ በርካታ የፈጠራ ምርቶች የተጎበኙ ሲሆን በዝግጅቱ ላይ የኮሌጁ አዛዥ ብርጋዲየር ጀነራል አበበ ዋቅቶላን ጨምሮ የኮሌጁ መምህራንና ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ ብዙአየሁ ተሾመ
ፎቶግራፍ ገነት አወቀ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
http://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
http://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
http://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

j
ኢትዮጵያ በየዘመኑ በታሪካዊ ጠላቶች እና በውስጥ ባንዳዎች ብትፈተንም፤ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት ፍላጎታቸውን እያከሸፈው ይገኛል።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
m
የኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የ71ኛ መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል። 
af
የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን አቅም የሀገራትን ዕድገትና ተፅዕኖ የሚወስን መሠረታዊ ኃይል ነው።       ዶክተር አለሙ ስሜ
m
የኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር የህልውና ጉዳይ እየሆነ በመምጣቱ በዘርፉ የሀገራችንን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው።    ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ
hu
የሁርሶ ኮንቲንጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት መሰረታዊ ወታደሮችን አሰመረቀ።
shu
ውትድርና ጀግንነትን እና ስብዕናን ተላብሶ ሠው ሰራሽና የተፈጥሮ መሠናክሎች ሳይበገሩት በፅናት መቆምን ይጠይቃል፦       ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታ

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።