ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር ያላት ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ ይቀጥላል፦   ክቡር ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ኀዳር 16 ቀን 2018 ዓ.ም

ኢትዮጵያና አሜሪካ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋትን ለማረጋገጥ በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዘዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን የተመራ ልዑክ ከኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ በአፍሪካ ቀንድ ሠላምና መረጋጋትን ለመፍጠር የቀጠናው ሐገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸውም ነው የተመላከተው።

ሁለት ሐገራት ወታደራዊን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ለበርካታ ዓመታት በትብብር እየሠሩ መምጣታቸውን ያነሱት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተች ትገኛለች ብለዋል።

ኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎቷ ለሠላማዊና ኢኮኖሚዋን ለመገንባት መሆኑን ያብራሩት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ከአሜሪካ ጋር ያለው ወታደራዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለፁት ኢትዮጵያ አልሸባብን ለማዳከምና የሽብር ሴራውን ለማክሸፍ የምትወስደውን የኃይል እርምጃ  አጠናክራ ትቀጥላለች።

ኢትዮጵያ በቀጠናው ፀጥታን ለማስፈን እየተጫወተች ያለችውን ሚና ያደነቁት የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄነራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን ሽብርተኝነትን በጋራ የመዋጋት ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ኢትዮጵያ በሠላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት የምታደርገውን መንገድ እንደሚደግፉ የገለፁት  የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዡ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይ ብትወጣ የበለጠ ለቀጠናው ሠላም ትሠራለች ብለው እንደሚያምኑ ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ በኩል ያሉ ፍላጎቶችንና በቀጠናው ሠላምን ለማረጋገጥ ስለያዘቻቸው ዕቅዶች ከዋሽንግተን ዲሲ ባለሥልጣናት ጋር እንደሚነጋገሩም ጠቁመዋል።
በዕለቱ “የአፍሪካ ቀንድ የሠላም ሁኔታ” በሚል ርዕስ በኮሎኔል መስፍን አውላቸው ጥናታዊ ፅሑፍ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ሁለቱ ሐገራት ስጦታ ተሰጣጥተዋል።

ዘጋቢ ውብሸት አንበሴ
ፎቶግራፍ አበረ አየነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ድረ-ገፅ
https://dfmc.mod.gov.et/

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ዩቲዩብ
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት  ቴሌግራም 
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ፌስቡክ
https://www.facebook.com/fdredefense.official

ወቅታዊ አጀንዳ

as1
ኢትዮጵያ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካዊያን ለመፍታት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን የመከላከያ ሚኒስትሯ ክብርት ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለፁ።
as
ኢትዮጵያ እና ኮንጎ ሪፐብሊክ (ብራዛቢል ) በወታደራዊ መስኮች ዙሪያ በትብብር ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ።
s6
በአምባሳደር ጄነራል ባጫ ደበሌ የተፃፈው ''የፀረ-ሽምቅ ውጊያ ጥበብ'' መፅሐፍ ተመረቀ።
mf
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አካል መሆን እንዳለባት የፈረንሣይ የምድር ኃይል አዛዥ ጄነራል ፒየር ሺል ገለፁ።
ay3
የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ።
Y
ፈረንሣይ ከኢትዮጵያ ጋር በወታደራዊ መስክ የበለጠ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን የፈረንሣይ ምድር ጦር አዛዥ ጄኔራል ፒየር ሺል ገለፁ።

ስፖርት

ኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

ለህገ መንግስቱ፣ ለሀገራችን መንግስትና ህዝቦች ፍፁም ታማኝ የሆነ፣ ጦርነትን የሚያቆም የልህቀትና የፍቅር ማዕከል የሆነ፣ በአስተማማኝ እና በብቃት በአገር አቀፍና በአለም አቀፍ ግዳጅ የሚያሳካ ዘመናዊ የመከላከያ ሰራዊት ማየት።

ማህበራዊ ሚዲያ